top of page




ምክር ቤቶች የህዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት መገለጫና ድሞ ክራሲ ያዊ ስርአት ማረጋገጫ አውራ ተቀቋማት ናቸው፡፡የከለላ ወረዳ ም/ቤት የወረዳው ከፍተኛው የስልጣን አካል እንደመሆኑ መጠን በወረዳው ህዝብና በህገ- መንግስቱ የተሰጠውን ሃላፊነት መሰረት በማድረግ በበላይ ም/ቤቶች ፀድቀው የወጡ ፖሊሲዎች፣ እስትራቴጅዎችና እቅዶች እንድሁም አሰራሮች በተገቢው መተግበራቸውንና ስራ ላይ መዋላቸውን ብሎም ለህዝብና ለሀገር እድገት በሚበጅ አቅጣጫ መተግበራቸውን በማረጋገጥ፣
-
ህገ-መንግስቱና ሌሎች ህጎች መከበራቸውን
-
የዜጎች ሰብአዊና ዴሞ ክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን
-
የህዝብና የመንገስት ሀብት እና በጀት በአግባቡ ለታለመለት አላማ መዋሉን
-
የመንግስት አገልግሎት ሰሚ ተቋማት አሰራር ግልጽነት፣ቀልጣፋነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ብሎም ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ መሆኑን በማረጋገጥ ለወረዳው ልማት መፋጠንና ለህዝቡ ተጠቃሚነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የላቀ ነው፡፡
bottom of page