top of page
ዜና ም/ቤት
Untitled16
Untitled15
Untitled14
Untitled13
Untitled12
Untitled11
Untitled10
Untitled3
Untitled4
Untitled5
Untitled6
Untitled7
Untitled8
Untitled9
Untitled2
Untitled1
afegubaye1
afegubaye

ም/ቤቱ ለተለያዩ የካቢኔ አባላት ሹመት ሰጠ

 

    የከለላ ወረዳ ም/ቤት ከታህሳስ 9-10 ባካሄደው የ2008 ዓ.ም 2ኛ መደበኛ ጉባኤው በተለያዩ መ/ቤቶች

የሃላፊዎችና  ምክትል ሃላፊዎች ሹመት ሰጥቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

   

 

     ሙሉ ስም                                      የተሰጠው  ሃላፊነት

1. አቶ አስናቀው ጥላሁን ባዩ          -   የአስ/ፀ/ጉ/ጽ/ቤት ሃላፊ

 

2. አቶ አፍዶል ሙላት ዳውድ         -  የአስ/ም/ቤትጽ/ቤት ሃላፊ

 

3. አቶይመር የሱፍ ለጋስ                -  የቅሬታሰሚ ኃላፊ

 

4. አቶ አህመድ አሰፋ ሁሴን             - የገ/ኢ/ል/ዋ ጽ/ቤት ም/ ሃላፊ

 

5. አቶ አለባቸው ዳውድ                 -  የቴ/ሙ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሃላፊ

 

6. አቶ ጀማል ሞላ ሀሰን                 - የትም/ጽ/ቤት ሃላፊ

 

7. አቶ መሀመድ ጡሃ                    - የትም/ጽ/ቤት ም/ ሃላፊ

 

8. አቶ ኢማም መሀመድ                 - የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ

 

9. ወ/ሮ ተዋበች አህመድ                - የሲ/ሰጽ/ቤት ሃላፊ

 

10. ወ/ሮ እጅጊቱ የሱፍ                 - የሲ/ሰ/ም/ ሃላፊ

 

11. ወ/ሮ ሰርካለም እሸቱ                - የመ/ኮሙ/ጉ/ጽ/ቤት ሃላፊ
 

12. አቶ ግዛው አማረ                     - የአካ/ጥ/መ/አስ/ጽ/ቤት ሃላፊ

 

13. አቶ ሸጋው አዲስ አለም              - የፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ

 

14. አቶ እንድሪስ ሙህየ                  - የህ/ስራማህ/ማሰ/ጽ/ቤት ሃላፊ
 

ከዚህ በተጨማሪም ለ3 ድርጂት ስራ አመራር አባላትም እውቅና ሰጥቷል፡፡
 

1. አቶ ሽመልሽ አሰፋ   - የህዝብተሳ/ጉ/አማካሪ ምክትል
 

2. ወ/ሮ ወሰኔ አወሉ    - የብአዴን ስልጠናና ሱፐርቪዥን
 

3. ወ/ሮ ኢክራም ሞላ   -የብአደን ሴቶች ሊግ

 

የበጀት ድልድሉ ፍትሃዊ ነው ተባለ

 

ከለላ ወረዳ የ2008 ዓ.ም የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ማስፈፀሚያ በጀት ለወረዳው ም/ቤት ቀርቦ ፀድቋል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የበጀት ቀመሩን ለም/ቤቱ  ሲያቀርቡ እንዳሉ ከተመደበው በጀት ከ86% በላይ የሚሆነው ለደመወዝ የሚውል መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ውጭ ያለውን በጀት ለዋና ዋና የልማትና መል/አስ ተግባራት ማስፈፀሚና ሌሎች ግደታ ወጪዎች እንድውል ተደርገጓል፡፡

የበጀት ምንጭ

  1. ከመንግስት የተመደበ 85772,440

  2. ከውስጥ ገቢ 2,83,500

  3. ከእርዳታ  2,83,500

  4. ጠቅላላ ድምር 89,448 674 ብር
     

የበጀት ድልድል
 

1. ለካፒታል ፕሮጀክቶች  ማስፈፀሚያ የተመደበ

  • ለአስተዳደር  ም/ቤት ቢሮ ግንባታ= 3437,207

  • ለግብርና  ጽ/በት ቢሮ  ግንባታ           697.420

  • ለተለያ ለንፁህ መጠጥ  ውሃ ግንባታ= 700.000

  • ለገበያ ማዕከል ግንባታ                 = 50.000

  • ለጥቃቅንና አነስተኛ ቤቶች ግንባታ=  300.000

  • ለምናያ ጤና ጣቢያ ግንባታ ማስጨረሻ=  40.000

ጠቅላላ ለካፒታል ፕሮጀክት የተመደበ =5,224,627 ብር

2. ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ =68,107,142 ብር

3. አድስ ለሚፈፀሙ ቅጥረሮች                 1.857,500 ብር

4. ለልዩ ል ሰነዶች ህትመት                 165,000 ብር

5. ለመን/መ/ቤቶች ስራ ማስጌጃ በጀት     12,440 676 ሆኖ ፀድቋል፡፡

 

በከለላ ወረዳ የመራጭ ተመራጭ መድረክ ተካሄደ

 

በወረዳው አቤት ውሃ ቀጠና የ019 አዲስ አምባ፤018 አቤት ውሃና 01አቤት ውሃ ከተማ ቀበሌ  ነዋሪዎች  በተገኙበት በአዲስ አምባ ቀበሌ የካቲት 14/2008 በተካሄደው የመራጭ ተመራጭ መድረክ ከ1200 በላይ መራጮች የተሳተፉ ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡   የመራጭ ተመራጭ መድረኩላይ የተገኙት በአብክመ ክልልም/ቤትየከለላ ወረዳ ህዝብ ተወካይና የደ/ወሎዞን ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን  ዳኘ የአካባቢው ነዋሪዎች በከባቢቸው የልማት ተግባራት እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አድን ቀው ይኸው በመልካም አስተዳደር አስተዳደርም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አፅንኦት ሰጥተው መክረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በበኩላቸው ተወካዩ አካባቢያቸው ድረስ መጥጠው በማወያየታቸው መደሰታቸውን ገልጸው በየደረጃው ባለው አካል መፈታት አለባቸው ያሏቸውን ጠልማት ጥያቄዎች  በተወካያቸው አማካኝነት እንዲቀርብላቸው አንስተዋል፡፡ነዋሪዎቹ ባቀረቡት ጥያቄዎች መካከል   የአቤት ውሃ  ከተማ የመብራት ዝርጋታ ስራ አለመፋጠን፣የአቤት ውሃ ከፍተኛ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ አለመጠናቀቅና ከንጹህ መጠጥ ውሃ ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል፡፡

የወረዳውን መስተዳድር ወክለው በውይይቱ ላይ የተገኙት የወረዳው ብአዴን የህ/ተሳ/አደ/አማካሪ አቶ ጌታቸው ደምሴ ከህ/ሰቡ በተነሱ የልማት ጥያቄዎችላይ በሰጡት አስተያየት እንዳሉት የተነሱት ሃሳቦች ተገቢና ትክክለኛ ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሰው  መንግስት ችግሮቹን ለመፍታት አቅም በፈቀደ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡የአቤት ውሃ ከተማመብራት ዝርጋት ስራ የተጓተተው ቀደምሲል በመንግስት በኩል የተጠናው ጥናት ባለአንድ ፌዝ በመሆኑና ይህም  አሁን ካለው ከከተማዋ አድገት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ወደ 3 ፌዝ ማሳደግ እንዲቻል የወረዳው መስተዳድር የህዝቡን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ በማቅረቡ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በቀጠናው ያለውን የውሃ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት በተደረገው ጥረት አሁን ላይ የክልሉ መንግስት ምላሽበመስጠቱ የጥናት ስራዉ ተጀምሯል  ካሉ በሑዋላ ነገርግን በየደረጃው ያሉ  የአመራር አካላት ተገቢትኩረት ሰጥተው በተፋጠነ ሁኔት ይሰራ ዘንድ ተወካዩ ባሉበት ችግሮቹ መነሳታቸው ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ የመራጭተመራጭ መድረኩ በየ6 ወሩ የሚካሄድ ሲሆን የም/ቤት አባላት ውክልናቸውን  የሚወጡበት ዲሞክራሲያዊ አሰራር  በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል  ሲሉ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

 

 ለዲሞክራሲዊ ስርአት መጎልበት የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ተባለ፡፡
 

 

 

 

 

 

 

 

 

በከለላ ወረዳ ም/ቤት ሴት የቀበሌ ምክር ቤት አባላትን  ተሳትፎ ለማጠናከር የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልየና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ ከየቀበሌው የተውጣጡ የሴት የም/ቤት አባላት ፎረም አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሴቶችን በሁለንተናዊ መንገድ ተሳትፎአቸው እንዲጎለብት ማድረግ የሴቶችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈም ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደታችን መፈጠን የጎላ ሚና አለው ተብሏል፡፡

    የአሁኑ ስልጠና መሰጠትም ሴት የቀበሌ ም/ቤት አባላት በየተወከሉበት ቀበሌ የቀበሌ ም/ቤቶች ወርሃዊ ጉባኤ ከመካሄዱ አስቀድሞ በመሰባሰብ እና በመምከር በጉባኤው ላይ ለሴቶች ጥቅም መከበርና ተሳትፎ መጎልበት የሚረዱ ውሳኔዎችን ለማስወሰንና በም/ቤቱ የላቀ ተሳትፎ ለማድረግ በሚረዱ ጉዳዮች ላይ በራሳቸው መድረክ በመምከር የጋራአቋም ይዘው ለመግባት ያስችላቸቃል፡፡

   የፎረም አስተባባሪዎቹ ስልጠናውን ከወሰዱ በሁዋላ ወደየተወከሉበት ቀበሌ ሲመለሱ ሴት የቀበሌ ም/ቤት አባላትን በመሰብሰብ ፎረማቸው በሚጠናከርበት ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በከለላ ወረዳ 35 የቀበሌ የሴቶች ፎረሞች የተቋቋሙ ሲሆን ከ4600 በላይ ሴት የም/ቤት አባላት በአባልነት ታውፈው ይገናሉ፡፡

 

ለቋሚ ኮሚቴዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ

 

 

 

 

 

 

 

 

የከለላ ወረዳ ምክርቤት በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ለሚገኙ የቀበሌ ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት   የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ምክር ቤቶችን ማጠናከር የልማትን ማፋጠን ዴሞክራሲን ማስፈን እንደሆነ የም/ቤቱ አፈግባኤ ጽ/ቤት አሳውቋል፡፡በመሆኑ በቀበሌና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የም/ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በም/ቤቶቹ የሚሰጡአቸውን የክትትልና ቁጥጥር ተልእኮዎች በአግባቡ ለመወጣት ይቻል ዘንድ የአባላቱን አቅም በስልጠና ማጎልበት አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው መሰጠቱን ከምክር ቤቱ የወጣው መረጃ አመልክቶአል፡፡

    በቀበሌ ም/ቤት ደረጃ የኢኮኖሚ ጉዳይ ፣የማህበራዊ ጉዳይ እና የህግ ፣ፍትህና አስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴዎች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን በወረዳው በሚገኙ 35 የቀበሌ ም/ቤቶች ስር የተቋቋሙ 105 የቋሚ ኮሚቴ አደረጃጀቶች ይገኛሉ፡፡ ስልጠናው የተሰጠው ከነዚህ ቋሚኮሚቴዎች ለተውጣቱ 105 የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ነው፡፡ ከስልጠናው በሁዋላ አባላቱ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው የተሰጣቸውን ውክልና በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ ያገኙትን እውቀት ይዘው የላቀ ስራ በማከናወን ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

 

በከለላ ወረዳ  የዋርጃ ቀጠና የቀበሌ ም/ቤት አፈጉባኤዎች የእርስበርስ መገማገሚያ የጋራ ፎረም አካሄዱ ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

የጋራ መገማገሚያ ፎረሙ የተዘጋጀው በ027 ሺነት ቀበሌ ም/ቤት ሲሆን የ027፣028 እና029 ቀበሌ ም/ቤት አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤዎች፣የየም/ቤቶቹ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ስራ አስኪያጆችና ሊቃነ መናብርት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

   በጋራ መገማገሚያ ፎረሙ የሁሉም ቀበሌ ም/ቤቶች የስራ እንቅስቃሴ፣የጉባኤ አፈጻጸም፣የየልማትና መል/አስ/ ተሳትፎና የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን የአዘጋጁ ቀበሌ የመስክና የቢሮ ተግባራት ጉብኝት ተካሂዶአል፡፡

   ፎረሙ እርስ በርስ የሚወያበትና ለጋራ ችግሮቻቸው የጋራ መፍትሄ የሚያፈላልጉበት የመማማሪያ መድረክ በመሆኑ ሁሉም ም/ቤቶች ወደ ተቀራራቢ የመፈጸም አቅም እንደሚያደርሳቸው በመታመኑ በየ2 ወሩ በየቀበሌዎቹ በዙር እንደሚደረግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

  የቀጣዩ አዘጋጅም የ029 ቤረዳ ቀበሌ ም/ቤት ሆኖ ተመርጧል፡፡

 

 

© 2016  የከለላ ወረዳ ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ጽ/ቤትphone  +251334510214

  • w-facebook
  • Twitter Clean
  • w-googleplus
  • w-youtube
bottom of page