top of page

የ2006 ዓም የከለላ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የሰዉ ሀብት ስራ አመራርና ልማት ደጋፊ የስራ ሂደት የግማሽ ዓመት የBSC ዕቅድ
መግቢያ
-
ባሳለፍነዉ በጀት አመት በሰዉ ሀብት ስራ አመራርና ልማት ደጋፊ የስራ ሂደት በርካታ ተግባራት ተከናዉነዋል፡፡
-
ከሰዉ ሀይል ስታስቲካል መረጃ አንጻር ከሰዉ ሀይል ስምሪት አኳያ በተለይም በቅጥር ፣በዝዉዉር፣ በደረጃ እድገት ወዘተ መመሪያና ደንብን መሰረት ያደረገ ተግባር ለመፈጸም የተደረገ ጥረት አበረታች ነዉ፡፡
-
የሰዉ ሀይል ስምሪትንና የመሳሰሉ ተግባራትን በብቃት ለመፈጸም በየደረጃዉ የተቋቋሙ ኮሚቴወችን በተግባር በማጠናከር የተጣለባቸዉን ኃላፊነት በብቃት እንድወጡ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡
-
በሰዉ ሀብት ስራ አመራርና ልማት ደጋፊ የስራ ሂደት የወረዱ መመሪያወችን ለማስከበር የተደረገ ጥረት የሻለ ነበር ብሎ መዉሰድ ይቻላል፡፡
-
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀጣይ መስተካከል ያለበት ጉዳይ የመረጃ አያያዝ፣ የሪፖርት ግንኙነት አግባብ፣ የአመለካከት ለዉጥ ማምጣት ተግባሮችን በቀጣይ መፍታት ያለባቸዉ ጉዳዮች ስለሆኑ ይህንን ክፍተት መሙላት የሚያስችል ስራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ለዚህም ይህ የ2006 ዓ.ም የስድስት ወር /6/ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
bottom of page